ርዕስ:- ጥንታዊዉ የኢትዮጵያ ቋንቋ እና ስነ-ፅሁፏ

By Mazoriatube777 122 views 1 year ago
ጥንታዊዉ የኢትዮጵያ ቋንቋ እና ስነ-ፅሁፏ © 2024 by Amanuel Etaa, Tesfaye Shiferaw, Entisar Mohammed, Kidist Melaku is licensed under Attribution-NonCommercial-NoDerivatives 4.0 International መነሻ ጥያቄዎች:- ፩)ፊደል ማለት ምን ማለት ነው? ፪)ግዕዝ ማለት ምን ማለት ነው?፫)የኢትዮጵያ ፊደሎች ስንት ናቸው? ፬)የኢትዮጵያ ፊደል ስንት ደረጃ አለው? ፭)በኢትዮጵያ ፊደል ውስጥ ስድስት የድምፅ መስጫ ምልክቶች አሉ እነማ ናቸው? መወያያ ሀሳቦች:- ፩)የፊደላት እና ቃላት አመሰራረት ወይንም አጠቃቀምን በተመለከተ በድሮ ጊዜ እንዴት ነበር ከየት ወዴት መጣ? ፪)የኢትዮጵያ ፊደላት እና ቃላቶችን፣የ አፃፃፍ ስርአቶችን እና ህግጋቶችን መቼ እና በምን ሁኔታዎች ነዉ ልንጠቀማቸዉ ሚገባዉ? ፫) ስለ ኢትዮጵያ ቋንቋ እና ስነ-ፅሁፍ ስናነሳ ጥንታዊዉ እዉቀቶቿ እና ህግጋቶቿን መጠበቅ እና መከተል ተገቢ ነዉ ወይስ አዲስ የቋንቋ ፍልስፍናን መከተል ነዉ የተሻለ ተገቢ የሚያደርገዉ? መግቢያ:- በትምህርት መልክ የ ኢትዮጵያን የቃላት መዝገብ እና የፊደላት የአጠቃቀም ስርአቶችን ማወቅ እና በአግባቡ መጠቀም ምን ያህል ጠቃሚ እና አንድን ሀሳብ ከነይዘቱ እና የጭብጥ ሀሳቡ ለማስተላለፍ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት በሰፊዉ ከማህበረሰቡ ጋር ለመወያየት ያደረግነዉ ጥረት ሲሆን። በቀድሞዉ ጊዜ የቃላት እና የፊደላት አመሰራረት/ አደረጃጀትበስነ- ፅሁፎቻችንበምንጠቀምበት ጊዜ ምክንያታዊ በሆነ ሁኔታ እንደነበር ብሎም ተያያዥነት ያላቸዉ ዉጤት እና መንስኤም መፍጠር በመቻሉ የጥንቱንም የትኢዮጵያን የቋንቋ ህግጋቶችን ማስቀጠል፣መማር፣ ማወቅና በስነ-ፅሁፍ አለም መተግበር መልእክትን ከነይዘቱ ለማስተላለፍ ጠቃሚ ሚና እንደሚጫወት የሚያምኑ የፅንፍ አካላት ሲኖሩ ፥ በተቃርኖ ደግሞ የቃላትና የፊደላት አጠቃቀም አለም በደረሰበት የስነ-ፅሁፍ የፍልስፍና ደረጃ ፊደላትንና ቃላቶችን የምንጠቀምበትን ሁኔታዎች የተግባቦት ክህሎትን ከማሳደግና ከመፍጠር ረገድ እንደ ሁኔታዎች መቀየር አስፈላጊ እንደሆነ ሁለተኛ የፅንፍ ወገኖች ደግሞ ይነሳሉ። ስለዚህ የኢትዮጵያን ቋንቋንና የስነ-ፅሁፍ አለምዋን በተመለከተ ከላይ በተነሱት ከነዚህ ሁለት የፅንፍ አመለካከቶች በመመርኮዝ ያሉንን ግንዛቤዎች ስንዳስስ ስለሀገራችን ቋንቋዎችን ስነ-ፅሁፍ አጥጋቢ መሰረታዊ እዉቀት እንኳን እንደሌለን ነዉ። በሳምንታዊዉም የዝግጅት ጥንክራችንም የተገነዘብነዉ ይህ የአዉቀት ማነስ በአብዛኞቻችን የኢትዮጵያ የወላጆች እንደሚስተዋል ነዉ። በዋነኝነት ለማህበረሰቡ ልናንፀባርቅ ያነሳሱን ሀሳቦች መጀመሪያ ከራሶቻችን ስንነሳ በምዕራባዉያን የስነ-ፅሁፍ ስርአቶች ላይ የተመሰረተ እዉቀት መሰረት ዕና እድገት ተፅእኖ ዉስጥ እንዳገኘንና በቤተሰቦቻችን፣ በእዉቀት አባቶች እና በምንኖርበት ማህበረሰብ ደግሞ ይህ ከምዕራባዉያን የተዋረስነዉ ፅነ-ፅሁፍን ክህሎቶች እንደ ስልጣኔ ጥግ በመዉሰዳቸዉ ስለ ሀገራችን መሰረታዊ የሆኑ የቋንቋ እዉቀቶችን እንድዘነጋ አድርገዉናል። በዚህ የፕሮግራም ዝግጅታችን እንደ ማጠቃለያ ሀሳብ ስለ መሰረታዊ ኢትዮጵያ የቋንቋ እዉቀቶች፣ ስለ አቡጊዳ፣ ግዕዝ፣ ፊደላቶችና ደረጆቻቸዉ ፣ስለ ድምፅ መስጫ ምልክቶቻቸዉ እና ስርአተ-ነጥቦቿ ምን ያህል እናዉቃለን እያልን ደግሞም ፊደል እና ቃላቶች ሲዛቡ የአንድ ህዝብ አላማም አብሮ እንደሚስት ካጠናናቸዉ መፃህፍት የጠቆሙንን ወደ እናንተ እያንፀባተቅን ባነሳናቸዉ የመወያያ ጥያቄዎች ዙሪያ ራሶቻችንን እየፈተንን ለቀጣዮ የሳምንታዊ ጥንቅሮቻችን እንዲጠባበቁን ከወዲሁ እየጋበዝናችሁ እነሰናበታችሁ። ደራሲ ፣ዜማ፣ ፀሀፊ ተዉኔት፣መስራች፣ እና የአለማቀፍ ግንኙነት :- አማኑኤል ኢተአ አዘጋጄ፣ አቅራቢ፣ ኘሮጂዮሰር እና ዳይሬክተር :- ተስፋዬ ሺፈራዉ አዘጋጅ ፣ጋዜጠኛ ፣ የፖድካስት ዝግጅት ሀላፊ አቅራቢ አና መስራች:- እንቲሳር መሀመድ ቃለመጠይቅ፣ ፕሮግራም አቅራቢ እና የሶሻል ሚዲያ ሀላፊ :- ቅድስት መላኩ
Latest Videos About Us FAQ Terms of Service Copyright Cookie Privacy Contact
© 2025 Febspot. All Rights Reserved.