የጥንቲቷ ኢትዮጵያ የስነ-ፅሁፍ ታሪክ

By Mazoriatube777 64 views 1 year ago
ከባለፈዉ የክፍል ዝግጅታችን የቀጠለ:- የጥንቲቷ ኢትዮጵያ የስነ-ፅሁፍ ታሪክ part 2 © 2024 by Amanuel Etaa, Tesfaye Shiferaw, Entisar Mohammed, Kidist Melaku is licensed under Attribution-NonCommercial-NoDerivatives 4.0 International ርዕስ:- የጥንቲቷ ኢትዮጵያ የስነ-ፅሁፍ ታሪክ ነፃነት በጥንቲቷ ኢትዮጵያ ታሪክ ዉስጥ እንዳጠናነዉ በሦስት ይከፈላል። 1. የግል/የራስ ነፃነት 2. የቤተሰብ/የማህበረሰብ ነፃነት 3. የመንፈስ ነፃነት ናቸዉ። መግቢያ:- ግዕዝ እንደ ነፃነት እና ኩራት መተረጎሙ፣ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የራሳቸውን ግንዛቤ፣ የማኅበረሰብና የቤተሰብ ነፃነት፣ ብሎም የገንዘብ ነፃነትን ለማግኘት ለሚያደርጉት ጥረት እንደ መሪ መርህ ሆኖ ያገለግላል። ኢትዮጵያውያን ጥንታዊ ታሪኮቻቸውን፣ ባህሎቻቸውን እና ስነ-ፅሁፎቻቸውን በማክበር እውነተኛ ማንነታቸውን አውጥተው በባህል፣ በፅናት እና በአንድነት ላይ የተመሰረተ ብሩህ የወደፊት ጉዞን መፍጠር ይችላሉ። ይህም ነገር ደግሞ እዉን ሆኖ በሀገራችን ሊንፀባረቅ የሚችለዉ ኢትዮጵያ በጥንታዊ ታሪኮቿ ተመዝግቦ እና ይኖር የነበረዉ ያ ራስን አዉቆ፣ ማንነትን ተገንዝቦ እና ሀላፊነቱን በቤቱ ብሎም በ ማህበራዊና በ ሀገራዊ ፍቅር ከ አንድነት ጋር ተንፀባርቆ ሲታይ ነዉ። ይህም በቀደምት ኢትዮጵያ ላይ ሰፍኖ የነበረ ሰላም፣ፍቅር፣አንድነት እና ነፃነት ለመመለስ መደረግ ያለበት ብለን ምናስበዉ፥ ወደ ታሪክ ጅማሪያችን እና መሰረት ልንመለስ ከቻልን ብቻ ነዉ ማለት ነዉ። ምክንያቱም የ አንድ ነገር ምንነት ሚታወቀዉ ጥንስሱ እና ጅምር መሰረቱ እስከታወቀ ከሆነ ድረስ ሀገራችን ኢትዮጵያ አሁን ለደረሰችበት ሁኔታ ያበቃት ጥንት አፅንቷት የነበረዉ ስርአት በተለያዮ መንግስታት፣ ግለሰቦች፣ ወይም በዉጣዊ እና ዉጫዉ ሊነሱ የሚችሉ ተፅእኖዎች ተደማምረዉ ነዉ ማለት ነዉ። ይህንን በጥልቅ ለመመርመር እና ለማጤን ታሪካችንን ግዜ ሰጥተን መመልከት ያስፈልጋል። የጥንት ታሪክ ባለቤት ፥ ለፈጠራ ጥበብ እና ለሳይንስ እድገት ጅማሬ ፥ ለስልጣኔ ተምሳሌት ሆና እና ተገኝታ የነበረችዉ ሀገራችን ኢትዮጵያ በአለም ላይ ተሰሚነት እንዲኖራት እና ተፅዕኖ ፈጣሪ አድርጓት የነበረዉ የነፃነት አለሟ የተመሰረተዉ ሀላፊነትን ተሸክሞ ፥ ቋንቋዉን አዉቆ ፥ ራስ ማንነቱን አዉቆ እና አክሮ ለቤቱ ሚቆም ህዝብ ስለነበረ ነዉ። ነፃነት ለኢትዮጵያዊያን ከ ፈጣሪያቸዉ የተቸራቸዉ ጥበባዊ መገለጫ ኖሮት በመቻቻል እንደ ህዝብ በጋራ ለሀገር በመቆም ለጋራ እድገት በኢኮኖሚ በአንድነት በመቆም ነዉ። ኢትዮጵያዉያን የዘር፣ የቋንቋ ፥የወሰን፣ የ ሀሳብ ፣ የ አላማ ልዮነት ያልነበሯቸዉ አንድ መልክ እና ድምፅ የነበሯቸዉ የ አፍሪካ ህዝቦች ናቸዉ። ስለዚህ የሀገራችንን ነባራዊ ስንመለከት መለስ ብለን ራሶቻችንን ፈትሸን ንቃተ-ህሊናዎቻችንን መፈተሽ አስፈላጊ ይመስለናል። ከላይ ያነሳናቸዉ መሰረታዊና አብይ ሀሳቦችን ስንመለከት ለምሳሌነት ልንጠቅስላቹ ያሰብናቸዉ ታሪኮች በ ምንሊክ ጊዜ እና በቀዳማዊ ንጉሰ-ነገስት ሀይለ ስላሴ የነበሩትን ታሪኮቻችንን በማስታወስ ነዉ። እነዚህንም የታሪክ ዘመናቶችን ስናስታዉስ ኢትዮጵያ ነፃነትዋ በአለም ገንኖ እና ባንዲራዋ ከፍ ብሎ ሲዉለበለብ ነበር። ነፃነታችን ከቅኝ ግዛት በዘለለ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይህ ግርማ ሞገስ እና የማንነት ኩራት በግንባሮቻቸዉ እና በአይኖቻቸዉ ጎልተዉ ይንፀባረቁ ነበር። በጥንት የነበረዉ የ ሀገር ፍቅር ከቆሎ ተማሪዉ እስከ መምህራኑ፣ ከምእመናን እስከ ቀሳዉስቱ፣ ከገበሬዉ እስከ ምሁራኖች ብሎም ለ ኢትዮጵያዊዉ የቆሙት ሀያላን መንግስታቶችን ድረስ ጨምሮ አንድ አርጎ ስለነበር ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊን መነጣጠል እስካይቻል ድረስ የአንድነታቸዉ መንፈስ እጅግ የጠነከረ እንደነበር አስተዉለናል። በአባቶቻችን ሲስተላለፍ የነበረዉ ይህ ነፃነትን የማስቀጠል እና የማስፈን ትግል በአደዋ ጊዜ ከቅኝ አገዛዝ ስርአት ነፃ እንድትወጣ አድርጓታል ። ይህም ኢትዮጵያ በቅኝ ስርአት ዉስጥ እንዳትወድቅና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተለይታ እንድትቀመጥ ያደረጋት ጉዳይ ህዝቦቿ በመንፈስ እና በነፃነት አንድ ስለነበሩ ነዉ ማለት ነዉ። መደምደሚያ :- ያንን ተምሳሌት ደግሞ በሀይለ ስላሴ የአገዛዝ ስርአት ወቅት ሲስተዋል የነበረዉ የሀገራችን ገናናነት በአለም ላይ ልንኮራበት እና ልንማርበት የሚገባ ይመስለናል ። ምክንያቱም የአፍሪካን ህብረት ምስረታ ምክንያት እና ለመላዉ አፍሪካ ነፃነት በአለም መድረክ ላይ ድምፅ እንድንሆን እና አፍሪካኖች አንድ ሰዉ ሊኖረዉ የሚገባዉን ነፃነት ለማስከበር ቆመዉ እና ዉጤት አምጥተዉ ስለነበር ነዉ። አሁንስ ነፃነታችን አለ ? አዎ …ከቅኝ ግዛት ድነናል …አእምሮአችንስ ነፃ ነዉ? እስቲ ቆም ብለን እናስብበት። ፀሀፊ ተዉኔት ፣ ደራሲ ፣ እና ዜማ :- አማኑኤል ኢተአ አዘጋጅ ፣ አቅራቢ፣ ኘሮጂዮሰር እና ዳይሬክተር :- ተስፋዬ ሺፈራዉ አዘጋጅ ፣አቅራቢ እና ጋዜጠኛ:- እንቲሳር መሀመድ ቃለመጠይቅ እና ፕሮግራም አቅራቢ:- ቅድስት መላኩ
Latest Videos About Us FAQ Terms of Service Copyright Cookie Privacy Contact
© 2025 Febspot. All Rights Reserved.